Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም የእስራኤል መንግስት በሲዳማ ክልል በሚደርጋቸው ድጋፎች እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
 
አቶ ደስታ የሲዳማ ህዝብ እንግዳ ተቀባይ እና የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ስጋት እንደሌለው ገልጸው÷የእስራኤል ዜጎች በክልሉ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
 
በክልሉ በርካታ የኢንቨስትመንት አማራጮች መኖራቸውን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ÷ክልሉ ከአዲስ አበባ ከተማ ያልራቀ፣ የአየር መንገድ እና የፍጥነት መንገድ ያለው መሆኑ ተመራጭ እንደሚያደርገውም ጠቁመዋል፡፡
 
የክልሉ መንግስት ባለሃብቶች በሚፈልጉት መልኩ የኢንቨስትመንት አማራጭ እንዳዘጋጀ እና በቱሪዝም ዘርፉ በሰፊው ለመስራት ቅድመ ዝግጅት እንዳጠናቀቀ መናገራቸውንም ከርዕስ መስተዳድሩ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቶ አለልኝ አድማሱ በበኩላቸው ÷ የክልሉ መንግስት ለባለሃብቱ በተደራጀ መልኩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ማዘጋጀቱን አድንቀዋል፡፡
 
ለእስራኤል ባለሃብቶች ስለ ሲዳማ ክልል ተጨባጭ ሁኔታ ግንዛቤ እንደሚፈጥሩ እና የእስራኤል ተሞክሮዎችን ለሲዳማ ክልል ግብዓት እንዲሆኑ በቅንጅት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.