በደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት ጄነራል ታባን ዴንጋይ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብቷል።
ልዑካኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይና የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ፍስሀ ሻውል አቀባበል ያደረጉላቸው መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታም ከተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር የሀገራቱን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ማሳደግ በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡