Fana: At a Speed of Life!

ከሰሞኑ “የሰብዓዊ መብት ጥሰት” በሚል የወጣው ሪፖርት ፖለቲካዊ ሸፍጥ አለበት – የሕግ ምሁራን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሰሞኑ “የሰብዓዊ መብት ጥሰት” በሚል የወጣው ሪፖርት ከሣይንሳዊ መንገድ ይልቅ ፖለቲካዊ ሸፍጥን የተከተለ ነው ሲሉ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተሠራው ምርምር የተሳተፉ የሕግ ምሁራን ተናገሩ፡፡

ምሁራኑ ለፋና ብሮድካስንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ አሸባሪው ህወሓት በርካታ ጥፋቶችን ማድረሱን የሚያረጋግጡ መረጃዎች ቢኖሩም በሪፖርቱ እንዳልታዩ ታልፈዋል፡፡

ልጃለም ጋሻው እንዳሉት÷ አሸባሪው ህወሓት በወረራ በቆየባቸው የአማራና አፋር ክልሎች የጅምላ ግድያ፣ ዝርፊያ፣ አስገድዶ መድፈርና ንጹሃን ላይ ያነጣጠሩ ጥፋቶችን ፈጽሟል፡፡

ደሞዝ ካሴ በበኩላቸው÷ ሰሞኑን የዓለም አቀፉ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሙያዎችኢትዮጵያን በተመለከተ ያወጡት ሪፖርት መሬት ላይ ያለውን እውነት የማይገልጽ፣ ሣይንሳዊ ዘዴዎችን ያልተከተለ መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

“ሪፖርት ተብሎ የተለቀቀው ልብ ወለድ በአማራና በአፋር ክልሎች የተፈፀመውን የአሸባሪው ህወሓት የጦር ወንጀል የካደ በሰሚ ሰሚ የቀረበ” ነው ብለዋል ምሁሩ፡፡

ይህ የሆነውም የሽብር ቡድኑን ነፃ ለማውጣትና በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር የተደረገ ሴራ መሆኑን ነው የጠቆሙት፡፡

በአፈወርቅ እያዩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.