ከ23 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድኑ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ከ 23 ዓመት በታች ዋንጫ ማጣርያ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ዛሬ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
አንደኛ ዙር የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታው ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚደረግ መሆኑን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የእግር ኳስ ቤተሰቡ ጨዋታውን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በነፃ በመታደም ለብሔራዊ ቡድኑ ድጋፍ እንዲሰጥም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥሪ አቅርቧል፡፡