Fana: At a Speed of Life!

የጉንፋን ህመም እና መፍትሄው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጉንፋን የላይኛው የመተንፈሻ አካልን የሚያጠቃ በቫይረስ የሚመጣ ሕመም ነው፡፡

ይህም ማለት አፍንጫን፣ የአፍ የውስጠኛው ክፍልን ፣ ላንቃን እንዲሁም ጉሮሮን የሚያጠቃ ቀለል ያለ ኢንፌክሽን መሆኑን የውስጥ ደዌ ሃኪም ዶክተር ቢኒያም መለሰ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ሃሳባቸውን አጋርተዋል፡፡

አንድ ሶስተኛ የሚሆነው ጉንፋንም በሪኖ ቫይረስ እንደሚመጣ የተናገሩት የህክምና ባለሙያው ሌሎችም በርካታ ጉንፋን አምጪ ቫይረሶች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡

ቫይረሶች ተላላፊ ናቸው ያሉት ዶክተር ቢኒያም ብዙ ጊዜ የምንኖርበት፣ የምንሰራበትና የትራንስፖርት መገልገያ አካባቢ የተጨናነቀ ከሆነ በቀላሉ ከአንዱ ወደ አንዱ ይተላለፋል ነው ያሉት፡፡

የጉንፋን ህመም ምልክቶችም አፍንጫ አካባቢ ፈሳሽ ነገር መኖርና ማቃጠል፣ሳል፣ አልፎ አልፎ ቀለል ያለ ትኩሳት፣ ብርድብርድ ማለት ጠንከር ሲልም ጠንከር ያለ ትኩሳት፣ የመገጣጠሚያና ጡንቻ ላይ ህመም መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን እነዚህ ምልክቶች የጉንፋን ብቻም ሳይሆኑ በሌሎች በቫይረስ የሚመጡ ህመሞች ምልክት ሊሆኑ ስለሚችሉ ሃኪም ማማከር ተገቢ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ህክምናውንም በተመለከተ በቤት ውስጥ ትኩስ ነገር በመጠጣት፣ በህመሙ ምክንያት ጉሮሮ ከቆሰለ ለማስታገስ ማር በመብላት ፣ ማስታገሻ መድኃኒቶችን በመውሰድ ፣ እረፍት በማድረግ ምልክቶቹ የሚቆዩበትን ጊዜ ማሳጠር እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም በሃኪም ትዕዛዝ እንደ ሽሮፕ ያሉ መድሃኒቶች እንደሚሰጡ ገልፀዋል፡፡

በፌቨን ቢሻው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.