Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን በምጣኔ ሐብት ለመተሳሰር በጋራ ለመስራት ተስማሙ

 

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን በመሰረተ ልማት ግንባታና በምጣኔ ሐብት ትስስር በጋራ ለመልማት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መከሩ።

 

የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ታባን ዴንግ ጋይ ከተመራው ልዑክ ጋር ተወያይተዋል።

 

በውይይታቸውም፥ ሁለቱ ሀገራት በመንገድ መሰረተ ልማት፣ ሀይል፣ ቴሌኮሙኒኬሽን፣ ውሃ፣ ትራንስፖርትና በሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ተሳስረው የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ለመስራት ከመግባባት ተደርሷል፡፡

 

የገንዘብ ሚንስትር አቶ አህመድ ሽዴ በውይይቱ ላይ፥ የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን የሁለትዮሽ ትብብር የቆየ መሆኑን ጠቁመው ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የኤሌክትሪክ ሀይል በማቅረብ፣ የመንገድ መሰረተ ልማት በመዘርጋትና በሌሎችም የኢኮኖሚ ዘርፎች ለመተባበር ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል ፡፡

 

አዲስ አበባን ከጁባ ጋር የሚያገናኘውን መንገድ ደረጃውን ለማሳደግ እና ለጋራ የኤሌክትሪክ ሀይልና በቴሌኮ ፕሮጀክቶች በጋራ ለልማት አጋሮች የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚጠይቁም ተመልክቷል።

 

የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንትና የልኡካን ቡድኑ መሪ ታባን ዴንግ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳናዊያን ሁለተኛ ሀገራቸው መሆኗን አንስተዋል።

 

አክለውም ለሁለቱ ሀገራት ህዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት ኢኮኖሚያዊ ትብብር ወሳኝ ነው ማለታቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.