Fana: At a Speed of Life!

የዓለም የቱሪዝም ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በአሶሳ ከተማ ከነገ ጀምሮ ይከበራል

 

 

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የቱሪዝም ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ35ተኛ ጊዜ “አዲስ እሳቤ ለቱሪዝም “በሚል መሪ ቃል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ከነገ ጀምሮ ይከበራል፡፡

 

ቀኑ ከነገ ጀምሮ እስከ መስከረም 15 ቀን 2015 ዓ.ም በድምቀት እንደሚከበር የተገለፀ ሲሆን÷አሶሳ ከተማም እንግዶቿን በመቀበል ላይ ትገኛለች።

 

በዚኅም የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በቱሪዝም መኒስቴር የቱሪዝም መዳረሻ እና መሰረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በዓሉን ለማክበር አሶሳ ከተማ ገብተዋል።

 

ዘርፉ በኮቪድ 19 እና በጦርነት ከደረሰበት ጉዳት እንዲያገግም የሚያስችል ሀገር አቀፍ የቱሪዝም ንቅናቄ እንደሚጀመርም ይጠበቃል።

 

የዓለም የቱሪዝም ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መከበሩ ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ለሚሰራው ስራ እንዲሁም የክልሉን የቱሪስት መስህቦች ከማስቀዋወቅ አንፃር አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም ተገልጿል።

በላምሮት የኔ ዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.