Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ የፌስቱላ ሆስፒታል መስራች ዶክተር ካትሪን ሐምሊን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ዶክተር ካትሪን ሐምሊን በ96 ዓመታቸው በትናንትናው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገልጿል።

ዶክተር ካትሪን ሀምሊን ፌስቱላ ኢትዮጵያ የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት በማቋቋም ከ60 ዓመት በላይ የፌስቱላ ህክምናን ሰጥተዋል።

በበጎ ተግባር ላይ ተሰማርተው የበርካታ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ችግርን የቀረፉት ዶክተር ካትሪን ሐምሊን የኢትዮጵያ የክብር ዜግነት እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የክብር ዶክትሬት ተበርክቶላቸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.