Fana: At a Speed of Life!

ለጨጓራ ህመምተኞች የሚመከሩ ምግቦች

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጨጓራ ህመም ከመጠን ያለፈ አልኮል በመጠጣት፣ ሲጋራ በማጨስ፣ ለረዥም ጊዜ በሚወሰዱ አንዳንድ መድሃኒቶች ፣በባክቴሪያ፣ በጭንቀት፣ ቅመም የበዛባቸውን ምግቦች በመመገብ ወይም በሌላ ምክንያት ሊከሰት ይችላል፡፡
የጨጓራ ህመም ከተከሰተ በኋላ ታማሚዎች ወደ ጤና ማዕከል በመሄድ ከሚያገኟቸው መድሀኒቶች በተጨማሪ አመጋገብን ማስተካከልን የህክምና ባለሙያዎች ይመክራሉ።
እንደ ህክምና ባለሙያዎች ገለጻ የጨጓራ ታማሚዎች እንደ ፍራፍሬ፣ አትክልት እና ባቄላ ያሉ በአሰር (ፋይበር) የበለጸጉ ምግቦችን እና የስብ መጠናቸው ዝቅ ያሉ እንደ ቀይ ስጋ፣ አሳ እንዲሁም የአሲድ መጠናቸው ዝቅ ያሉ ምግቦችን ቢመገቡ ህመሙን ያስታግስላቸዋል።

 

በተጨማሪም ፍራፍሬዎች ለጤና ጠቃሚ የሆኑ ቫይታሚኖችን ፣ አሰር እና አንቲ ኦክሲደንቶችን ስለሚይዙ በዕለት ከዕለት አመጋገብ ማካተት ጠቃሚ እንደሆነ ይመከራል፡፡

 

እንደ ፖም እና ሃብሃብ የመሳሰሉት ፍራፍሬዎች ለጨጓራ ህመምተኞች ተስማሚ የምግብ አይነቶች ሲሆኑ እንደ ብርቱካን ያሉ አሲድ ያላቸው ፍራፍሬዎች ደግሞ እንዲወሰዱ አይመከርም፡፡

 

የተለያዩ የአትክልት አይነቶችን መመገብ ለጨጓራ ህመምተኞች ተስማሚ ሲሆን በምግብ አዘገጃጀት ላይ የሚጨመሩ እንደ ነጭ ሽንኩርት እና የተለያዩ ማጣፈጫ ቅመሞችን መቀነስ መልካም መሆኑንም ነው ባለሙያዎቹ የሚመክሩት።

 

በተቻለ መጠን ቅመም ያልበዛባቸውና ቀለል ያሉ ምግቦችን መመገብ ከዚህ ባለፈም ውሀ መጠጣትም ለሰውነታችን በጣም ጠቃሚ ሲሆን እንደ ቡና ፣ሻይ እና ለስላሳ እንዲሁም የአልኮል መጠጦች የጨጓራ ህመም ያለባቸው ሰዎች እንዲወስዷቸው አይመከርም፡፡

 

ምንጭ ÷ ሄልዝ ላይን

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.