Fana: At a Speed of Life!

የጅግጅጋ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ 75 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ900 መቶ ሚሊየን ብር ወጪ እየተገነባ ያለው የጅግጅጋ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት 75 ከመቶ መድረሱ ተገለፀ፡፡

2ኛው ዙር የጅግጅጋ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማንና የክልሉ የውሃ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀሰን መሀመድ ጎበኝተዋል።

የውሃ ፕሮጀክቱ ግንባታ የሥራ አፈፃፀሙ ያለበትን ደረጃ በተመለከተም ከፕሮጀክቱ የሥራ ሂደት ባለሙያዎች ጋር ተወያይተዋል።

የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታው ከተጀመረ አንድ አመት በላይ መሆኑን የተናገሩት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፥ በዋናነት የሚቀረው የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራ መሆኑም ነው የተገለጸው።

በጅግጅጋ ከተማ ካለው የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር አንፃር ፕሮጀክቱ በፍጥነት ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ የውሃ ፕሮጀክቱን ግንባታ እያከናወነ የሚገኘው የቻይናው ሲሲኢሲሲ ኩባንያና የክልሉ ውሃ ልማት ቢሮ ጋር ተነጋግረው አቅጣጫ ማስቀመጣቸውንም ተናግረዋል።

የውሃ ፕሮጀክቱ የተለያዩ ተግዳሮቶች እንዳሉበት የገለፁት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን፥ በዚህ የተነሳ ስራው መጠናቀቅ ከሚገባው ጊዜ ተጨማሪ 7 ወራት እንዲጨምር ማድረጉንም ነው የገለጹት።

የክልሉ የውሃ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀሰን መሀመድ በበኩላቸው ፥ በአሁኑ ወቅት የከተማው የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን 20 ከመቶ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

2ኛው ዙር የጅግጅጋ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ሲጠናቀቅ፥ የክልሉን የውሃ ሽፋን ወደ 50 ከመቶ ከፍ ለማድረግ እንደሚያስችል ከሶማሌ ክልለ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.