Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ- ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር መጠናከር የሀገራቱን የንግድ እንቅስቃሴን ያቀላጥፋል- አቶ አህመድ ሺዴ

 

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ- ጂቡቲ ስታንደርድ ጌጅ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር የሁለቱን ሀገራት የንግድ እንቅስቃሴ እንደሚያቀላጥፍ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ገለጹ።

 

የአክሲዮን ማህበሩ የስራ አመራር ቦርድ የምክክር መድረክ ዛሬ በድሬዳዋ ከተማ በተጀመረበት ወቅት ሚኒስትሩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የአክሲዮን ማህበሩ መጠናከር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ እንደሚያቀላጥፍ ተናግረዋል።

 

ይህንን ስራ አጠናክሮ ለማስቀጠል በተቀናጀ መልኩ መስራት ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትሩ፥ በተለይ ከሰላምና ፀጥታ አንፃር እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች መጎልበት እንዳለባቸውም አመላክተዋል።

 

በምክክር መድረኩ የድርጅቱ አፈጻጻም የሚገመግም ሲሆን፥ የሀይል አቅርቦት፣ የፀጥታና አደረጃጀት ጉዳዮች እንደሚዳሰሱም ይጠበቃል።

 

እንዲሁም ከሁለቱ ሀገራት የተወከሉ የቦርድ አባላትና የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊዎች የባቡር ዘርፍ አቅም ግንባታ ስራ የደረሰበትን ደረጃ ምልከታ እንደሚያደርጉ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.