Fana: At a Speed of Life!

የሀድያ ብሄር ዘመን መለወጫ”ያሆዴ” በ“ዩኔስኮ” እንዲመዘገብ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀድያ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል “ያሆዴ” በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፥ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) እንዲመዘገብ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የሀዲያ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል ” ያሆዴ” በዞኑ ከተማ ሆሳዕና “ሀዲይ ነፈራ” ተከብሯል።

በሀዲያ ዘመን አቆጣጠር ቀመር የመጀመሪያው በሆነው ወር “ሞሶሮኦ” የሚከበረው ያሆዴ÷ከአሮጌው አመት ወደ አዲሱ አመት መሸጋገሪያ፣  በውሃ ሙላት ተራርቆ የቆየ ወዳጅ ዘመድ የሚገናኝበት፣ የተቀያየመ ሰው እርቅ አውርዶ አዲሱን አመት የሚቀበልበት በዓል መሆኑ ተገልጿል።

በበዓሉ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬና ሌሎች ከፍተኛ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በተለያዩ ባህላዊ እሴቶች ታጅቦ የሚከበረው ያሆዴ÷ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የማይዳሰስ ወካይ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

በበዓሉ ላይ ከሲዳማ፣ አፋር፣ ሀላባ፣ ማረቆ፣ ወላይታ፣ ጋሞ እና ከሌሎችም ብሄር ብሄረሰቦች ተጋባዥ ልዑካን እንዲሁም የአጎራባች ዞኖች ዋና አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል።

ያሆዴ ስለሰላም የሚሰበክበት እና ለመጪው ጊዜም የሚፀለይበት እንደመሆኑ በመላው ኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን የሀገር ሽማግሌዎች ጸሎት አድርገዋል፡፡

በሞሊቶ ኤልያስ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.