Fana: At a Speed of Life!

የመስቀል ደመራ በዓል በሐረሪ ክልል በድምቀት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል ደመራ በዓል በሐረሪ ክልል በድምቀት ተከብሮ ውሏል።

በበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መላከ ገነት ቀሲስ ንጋቱ ደሳለኝ ÷ የመስቀል ደመራ በዓል የአንድነትና የነጻነት አርማ በመሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓሉን በድምቀትና ባማረ መልኩ ታከብረዋለች ብለዋል።

ስለሆነም የመስቀል ደመራ በዓል የአንድነት፣ የሰላምና የመቻቻል በዓል በመሆኑ ህዝበ ክርስቲያን በዓሉን በጋራ፣ በመተባበር መንፈስና የሀገሩንና የወገኑን ሰላም በመጠበቅ ሊያከብረው ይገባልም ነው ያሉት፡፡

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ በበኩላቸው÷ የመስቀል ደመራ በዓል የሰላምና የአንድነት በዓል ነው ሲሉ አውስተዋል፡፡

በተለይ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ከውስጥም ከውጪም የገጠማትን የተለያዩ ጫናዎች ለማሸነፍ በጋራና በአንድነት ልንቆም ይገባል ብለዋል፡፡

በህዝቦች መካከል ለዘመናት የቆዩትን መልካም እሴቶችን አጥብቆ የመያዝ ምሳሌነቱን ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

የክልሉን ሰላም ለማስቀጠል፣ የእርስ በርስ ግንኙነቶችን በማጠናከርና የጋራ እሴት የሆነውን መቻቻል ይበልጥ ማሳደግ ይገባል ያሉት ሃላፊው ÷ የሃይማኖት ተቋማትም ተከታዮቻቸውን በጎ ምግባርና መልካም ተግባራትን ማስተማር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

በአከባበር ስነ ስርዓቱ ከሁሉም ደብር የተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች፣ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የእምነቱ ተከታዮች መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.