Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ምክትል ስራ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ምክትል ስራ አስፈጻሚ ሎፔዝ ዳሲልቫ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ አምባሳደሯ  ወቅታዊ የኢትዮጵያ  ሁኔታን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በተለይም መንግስት በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ  ለመቋጨት ፍላጎቱን ማሳየቱን እና በተቃራኒው ሽብርተኛው ህወኃት የሰብዓዊ እርዳታዎችን ከህዝብ በመንጠቅ ለጦርነት ዓላማው እያዋለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ይህንን ኃላፊነት የጎደለውን የህወኃት የሽብር እንቅስቃሴና ተግባር አለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያወግዝ አምባሳደሯ ጠይቀዋል፡፡

ምክትል ስራ አስፈፃሚው በበኩላቸው÷ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝና በቀጣይ ሰብዓዊ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፃቸውን ከሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.