Fana: At a Speed of Life!

የእንግሊዝ የሃገር ውስጥ እግር ኳስ ውድድሮች ተራዘሙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር የሚያስተዳድራቸው ውድድሮች እስከ መጭው ሚያዚያ ወር መጨረሻ ድረስ ተራዘሙ።

የእንግሊዝ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል የፕሪሚየር ሊጉን ጨምሮ በሌሎች የሃገር ውስጥ ውድድሮች ቀጣይ ሁኔታ ላይ በዛሬው እለት ከክለቦች ጋር ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

በውሳኔው መሰረትም ፕሪሚየር ሊጉን ጨምሮ ሻምፒዮን ሺፕ እና ሌሎች የሃገር ውስጥ ውድድሮች ቢያንስ እስከ ፈረንጆቹ ሚያዚያ 30 ድረስ እንዲራዘሙ ወስኗል።

እንዲሁም ማህበሩ የሚያስተዳድረው የሴቶች እግር ኳስ ውድድርም የማይካሄድ ይሆናል።

ውሳኔው አሁን ላይ የዓለም ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመከላከል ያለመ መሆኑንም ማህበሩ አስታውቋል።

የተለያዩ ሃገራት የውስጥ እግር ኳስ ውድድሮች በኮሮና ቫይረስ ስጋት ሳቢያ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘማቸው ይታወሳል።

የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበርም ሰኔ ወር ላይ ሊካሄድ የነበረውን የአውሮፓ ዋንጫ ለአንድ አመት ያራዘመ ሲሆን፥ አህጉራዊ የክለቦችን ውድድሮችም ላልተወሰነ ጊዜ አራዝሟል።

ምንጭ፦ ስካይ ስፖርት

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.