Fana: At a Speed of Life!

በቤልጂየም በአረጋውያን መርጃ መዕከል የሚኖሩ ዜጎች በሮቦት የቪዲዮ ጥሪ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተገናኝተዋል

አዲስ አበባ፣መጋቢት 10፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤልጂየም በአረጋውያን መርጃ መዕከላት የሚኖሩ ዜጎች በሮቦት የቪዲዮ ጥሪ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘት መቻላቸው ተሰምቷል።

የቤልጂየም መንግስት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሀገሪቱ የሚገኙ የአረጋውያን መርጃ ማዕከላት ለጎብኚዎች ዝግ እንዲሆኑ ወስኗል።

ይህን ተከትሎም የሀገሪቱ ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በመርጃ ማዕካላት የሚኖሩ አረጋውያንን ከቤተሰቦቻቸው ጋር በቪዲዮ ጥሪ ማገናኛት የሚያስችል ሮቦት ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ይህም አረጋውያኑ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ጠብቀው እንዲኖሩ የሚያስችል መሆኑ ታምኖበታል።

የ 1 ነጥብ 2 ሜትር ቁመት ያላቸው ሮቦት ማሽኖች ክፍሎቹን በማሰስ በፌስ ቡክ ሜሴንጀር የቪዲዮ ጥሪዎች በማድረግ ያገናኛሉም ነው የተባለው፡፡

ለዚህም ዞራቦትስ የተባለው ኩባንያው መጀመሪያ ላይ 60 ሮቦቶችን ድጋፍ ማድረጉን ጠቁሞ÷ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ሮቦቶችን ማዘጋጀቱንም አስታውቋል፡፡

የኦስታንት ከተማ አስተዳደር የአረጋውያን መርጃ ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ኔል ቫንዊዬል በበኩላቸው÷ ሮቦቶቹ አረጋውያኑን ከውጭው ዓለም እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር በማገናኘት ትልቅ እገዛ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

የቤልጂየም መንግሥት የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት የአረጋውያን መርጃ ማዕከላትን ለጎብኝዎች ዝግ ከማድረግ ጀምሮ ትምህርት ቤቶችን በመዝጋት የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡

በሀገሪቱ እስካሁን 1 ሺህ 85 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፥ አምስት የሚሆኑት ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ምንጭ፡-ሬውተርስ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.