Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 4ኛው የኢሬቻ ፎረም እና የዋዜማ ዝግጅት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በጋራ ያዘጋጁት አራተኛው የኢሬቻ ፎረም እና የዋዜማ ዝግጅት በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ፡፡

በነገው ዕለት ለሚከበረው የኢሬቻ ክብረ በዓል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢሬፈና የሚከናወንበትን ስፍራ ጨምሮ የተለያዩ የእንግዶች መዳረሻዎችን በማፅዳት ለክብረ በዓሉ ዝግጁ ማድረጉን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በከተማዋ መከበር ከተጀመረ አራት ዓመት የሆነው ኢሬቻ ዘንድሮ ባሕላዊ እሴቶች፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ይከናወናል።

በዝግጅቱ ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ የፖናል ውይይትና የተለያዪ በዓሉን የሚዋጁ የኪነጥበብ ስራዎች የሚቀርቡበት ይሆናል።

በፎረሙ ላይ አባ ገዳዎች፣ ሐደ ሲንቄዎች፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም ሚንስትሮች እና የተለያዩ ክልሎች ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.