Fana: At a Speed of Life!

የሆረ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓልን ለመታደም እንግዶች ቢሾፍቱ እየገቡ ነው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ነገ የሚከበረውን የሆረ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል ለመታደም ከተለያዩ የኦሮሚያና ሌሎች አካባቢዎች የመጡ እንግዶች ቢሾፍቱ እየገቡ ነው፡፡

የከተማዋ ጎዳናዎች የተዋቡ ባሕላዊ አልባሳትን በለበሱና የተለያዩ ዜማዎችን በሚያሰሙ ወጣቶችና ታዳሚዎች አሸብርቀዋል።

በዓሉ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ፎሌዎች፣ የፀጥታ ኃይሎችና የከተማዋ ነዋሪዎች በትብብር እየሠሩ እንደሚገኙም ታውቋል።

የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ሆቴሎች እና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ለበዓሉ የመጡት እንግዶቻቸውን እየተቀበሉ መሆኑንም በስፍራው የሚገኙ ባልደረቦቻችን ተመልክተዋል።

የሆረ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል በርካታ ታዳሚዎች በሚገኙበት መርሐ ግብር ነገ ማለዳ በሐይቁ ዳርቻ በአባ ገዳዎች ምርቃትና መልካም ምኞት ታጅቦ ይከበራል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፥ በነገው እለት በቢሾፍቱ ከተማ የሚከበረው የሆረ ሀርሰዴ ኢሬቻ ልክ እንደ ሆረፊንፊኔው፥ እሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

በሐብታሙ ተክለ-ሥላሴ እና አብርሃም ፈቀደ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.