Fana: At a Speed of Life!

አልማ አርአያነት ያለው ተግባር እያከናወነ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) የአማራ ክልልን የልማት ክፍተቶች በራስ አቅም በመሙላት አርአያነት ያለው ተግባር እያከናወነ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ገለጹ።

አልማ 14ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውንና የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት በባሕርዳር ከተማ እያከበረ ነው፡፡

ዶክተር ይልቃል ከፋለ በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ አልማ ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጡ የጤና፣ የትምህርት እና ሌሎች ተቋማትን በመገንባት አርአያነት ያለው ተግባር እያከናወነ ነው ብለዋል፡፡

በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በሙያ ክህሎት ስልጠናና ሌሎች ተግባራት ወጣቶችና ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትን ማከናወኑንም አብራርተዋል፡፡

በተለይም የቅድመ መደበኛ ትምህርት እንዲስፋፋ አልማ እያከናወነ ያለው ሥራ ለትምህርት ጥራት መጠበቅ የጎላ አስተዋፅኦ አለው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የልማት ችግራችንን በዘላቂነት መፍታት የምንችለው አንድ ሆነን በመንቀሳቀስና መደጋገፍ ስንችል ነው ያሉት ዶክተር ይልቃል÷ ለዚህ ደግሞ አልማ የያዘው መንገድ አዋጭ ነው ብለዋል፡፡

የክልሉ ተወላጆችና የልማት ደጋፊዎች በገንዘባቸውና በዕውቀታቸው አልማን በማገዝ የክልሉ ልማት ለማፋጠን በጋራ እንዲሠሩ ጠይቀዋል፡፡

የአልማ ዋና ስራ አስፈጻሚ መላኩ ፈንታ እንደገለጹት÷ አልማ የክልሉ መንግሥት የማይገባባቸው የልማት ዘርፎችን ለይቶ በመሙላት ሕዝቡን የልማት ተጠቃሚ እያደረገ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.