Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ እርምጃ የተወሰደባቸው ተቋማት 767 ደረሱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 767 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን የከተማ አስተዳደሩ ንግድ ቢሮ ገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ በከተማዋ መታዩቱን ተከትሎ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እና የአቅርቦት ችግር እንዳይፈጠር ግብረ ሃይል በማቋቋም የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል።

ባለፉት ቀናት በተዋቀረው ግብረ ሀይል ውጤታማ ስራ የተከናወነ ሲሆን፥ እስከ ዛሬ ድረስ ከ14 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ ቁጥጥር እና ክትትል መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

በቁጥጥሩም 11 የምርት አይነቶች እና 12 ፋርማሲዎችን ጨምሮ በ767 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ተናግረዋል።

ተገቢ ያልሆነ ዋጋ ጭማሪ ለማድረግ፣ በጋራ ዋጋ የመወሰን፣ ምርት የማከማቸት እና የመደበቅ እንዲሁም በተለያዩ ምርቶች የዋጋ ንረትና ሰው ሰራሽ እጥረት በሚያስከትሉ ስራዎች በተሰማሩ የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መወሰዱንም ኃላፊው ገልጸዋል።

እርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል ወፍጮ ቤቶች፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ተቋማት፣ ሸቀጣ ሸቀጥ ንግድ ተቋማት፣ ፋርማሲዎች እና በበርበሬ ንግድ የተሰማሩ ነጋዴዎች መሆናቸውንም አመላክተዋል።

ችግር በፈጠሩ ነጋዴዎች ላይ እንደጥፋታቸው አይነት ከአስተዳደራዊ ጀምሮ እስከ ማሸግ የደረሰ እርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑንም ነው የቢሮ ኃላፊው የተናገሩት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.