Fana: At a Speed of Life!

ግጭቱን ለመፍታት መንግሥት የሚወስዳቸውን ሁሉንም ዓይነት የመፍትሔ እርምጃዎች አጠናከሮ ይቀጥላል – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ግጭቱን ለመፍታት መንግሥት ሲወስዳቸው የቆያቸውን ሁሉንም ዓይነት የመፍትሔ እርምጃዎች አጠናከሮ እንደሚቀጥል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

አገልግሎቱ ባወጣው የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ንግግሩን የሚመሩ አካላትን፣ ቀንና ስፍራን አሳውቆ የሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ይፋዊ ጥሪ ማቅረቡን አስታውቋል።

የአፍሪካ ኅብረት ግብዣ መንግሥት ከዚህ በፊት ያቀረባቸውን አቋሞች የጠበቀ ሆኖ መገኘቱንም አገልግሎቱ ባወጣው መረጃ ጠቅሷል።

ንግግሩ በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ብቻ እንዲሆንና ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲደረግ መንግሥት አቋሙን ሲገልጽ መቆየቱንም አስታውሷል።

ግጭቱን ለመፍታትም መንግሥት ሁሉንም ዓይነት የመፍትሔ እርምጃዎች ለመውሰድ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ጠቅሶ፥ ወደፊትም ይህንኑ አጠናከሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.