Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ካቢኔ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ካቢኔው በስብሰባው በክልሉ የመስኖ ስንዴ ልማትን ለማስፋት በዘር እና በግብዓት አቅርቦት ዙሪያ የመንግሥት፣ የአርሶ አደሩና የባለሃብቶች ሚና ምን መሆን እንደሚገባው በቀረበው ሃሳብ ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

በተጨማሪም በሥራ ዕድል ፈጠራ ኤጄንሲ በማህበር ለተደራጁ ወጣቶች ተገዝተው ሳይከፋፈሉ የቀሩ 120 ጄኔሬተሮችን ለተጠቃሚዎች ማድረስ እንደሚገባ ለመወሰን በቀረበው አጀንዳ ላይ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር  አሻደሊ ሀሰን ውሳኔዎችን አስመልክተው ባደረጉት ንግግር  ÷  የመስኖ ስንዴ ልማት እንደ ሀገርም ትኩረት መሰጠቱን እና በስንዴ ምርት ዙሪያ ተስፋ ሰጭ ለውጦች መመዝገባቸውን ገልፀዋል፡፡

እንደ ክልልም በዘርፉ የታቀደውን የስንዴ ምርት ለማሳካት ሁሉም ርብርብ ሊያደርግ እንዲሚገባ ማስገንዘባቸውን   ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.