Fana: At a Speed of Life!

የእጅ ስልካችንን በማጽዳት ራሳችንን እንዴት ከኮሮና ቫይረስ መከላከል እንችላለን?

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤታችንም ሆነ በምንሰራበት ስፍራ በተደጋጋሚ የእጅ ንክኪ የሚበዛባቸው ስፍራዎችን ማጽዳት ከቫይረሱ የመከላከያ መንገዶቹ መካከል አንዱ ነው።

ስልክዎን በኪስዎ፣ በቦርሳዎ አንዳንዴም ወደ መፀዳጃ ቤት ሲሄዱ ይዘውት ይሄዳሉ።

ምን ያህል አደገኛ ተህዋሲያንን (ጀርሞችን) ስልክዎ ብቻ ተሸክሞ እንደሚገኝ አስበውታል?

የኮሮና ቫይረስን ስላለመያዙ ምን ያህል እርግጠኛ ነዎት? ስለሆነም ስልካችንን ለማጽዳት 70 በመቶ አልኮል ያለው ዋይፐር መጠቀም የሚቻል ሲሆን በረኪና ግን አይመከርም ።

ከዚያም ባለፈ ቀላል ሳሙናና ውሃም ለማጽዳት እንደሚያገለግልም ባለሙያዎች ይመክራሉ።

በለንደን ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ማይክሮባዮሎጂስት የሆኑት ዶ/ር ሌና ሲሪክ÷ ስልክዎን ለማጽዳት ከቻርጀሩ መንቀል፣ መሸፈኛ ካለው ማውለቅ ቅድሚያ ልትወስዷቸው የሚገባው ዋንኛ ተግባር መሆን አለበት ሲሉ ይመክራሉ።

ዋና ዋና የሚባሉት የስልክ አምራቾች ስልካችንን ለማጽዳት ኬሚካሎች፣ ለእጃችን ማፅጃነት የምንጠቀምባቸው ሌሎች የጽዳት መጠበቂያዎች እንዲሁም ሸካራ ነገርን ለማጽዳት የሚያገለግሉ ዋይፐሮችን መጠቀምን አይመክሩም።

ለዚህ ደግሞ ምክንያታቸው የስልክዎን ስክሪን መከላከያ ይጎዳሉ አልያም ያወድማሉ የሚል ነው።

ስለሆነም በቀላሉ በውሃና በሳሙና በተነከረ ጥጥ ወይም ከጥጥ በተመረተ ጨርቅ የስልክዎን ስክሪንም ሆነ ጀርባ እንዲሁም ጎኖች ማጽዳት በቂ መሆኑን ዶ/ር ሌና ይናገራሉ።

በዚህ ወቅት ግን የሚያጸዱበት ፈሳሽ በስልኮቹ ክፍተቶች በኩል እንዳይገባ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበትም ነው አንስተዋል፡፡

በአግባቡ ከወለወሉ በኋላ በለስላሳ ጨርቅ ማድረቅ አስፈላጊም ነው ብለዋል፡፡

በዚህ ሁሉ ስልክዎን ካፀዱ በኋላ ባልታጠበ እጅዎ ከሆነ የሚጠቀሙት መልሶ ስልክዎ በጀርሞች ይሞላል ስለሆነም እጅን በየጊዜው መታጠብ አስፈላጊ ነው።

 

ምንጭ፦ ኢመደኤ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.