Fana: At a Speed of Life!

በቦረና ዞን ነዋሪዎችን የመብራት ተጠቃሚ ያደረገው ታዳጊ የ200 ሺህ ብር ሽልማት ተበረከተለት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ዋጪሌ ወረዳ ከተለያዩ ቁሶች የኤሌክትሪክ ኃይል በመፍጠር ነዋሪዎችን የመብራት ተጠቃሚ ያደረገው ታዳጊ የ200 ሺህ ብር ሽልማት እና እውቅና ተሰጥቶታል፡፡
 
የአካባቢውን ነዋሪዎች የመብራት ተጠቃሚ ያደረገው የ8ኛ ክፍል ተማሪው አዳን ሁሴን÷ ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሽመልስ አብዲሳ እጅ ነው የ200 ሺህ ብር ሽልማት የተቀበለው፡፡
 
የቦረና ዞን ዋጪሌ ወረዳ የዌብ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው አዳን ሁሴን ÷ በትምህርት ቤት ያገኘውን እውቀትና የራሱን የፈጠራ ክህሎት በመጨመር የአካባቢውን ነዋሪዎች የመብራት ተጠቃሚ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
 
ርዕሰ መስተዳደር ሽመልስ ÷ ባለ ልዩ ተሰጥኦ ዜጎች ሲበዙ በሀገር ዕድገት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖራቸው አንስተዋል፡፡
 
የኦሮሚያ ክልል መሰል የፈጠራ ክህሎት ያላቸውን ታዳጊዎች ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑንም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ ያረጋገጡት፡፡
 
አዳን ሁሴን በአከባቢው በፈጠረው የኤሌክትሪክ ሃይል በወር እስከ 7 ሺህ ብር ገቢ እያገኘ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
 
በገመቹ ቤኩማ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.