Fana: At a Speed of Life!

አንጋፋው የስፖርት ሰው ፍቅሩ ኪዳኔ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኝነት ታሪክአንጋፋው የስፖርት ሰው ፍቅሩ ኪዳኔ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኝነት ታሪክ የእግር ኳስ ጨዋታን በቀጥታ በሬዲዮ በማስተላለፍ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

አቶ ፍቅሩ በኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኝነት ታሪክ ፈር ቀዳጅ ከሚባሉ ግለሰቦች አንዱ እንዲሁም በስፖርት ጋዜጠኝነት፣ አመራርነት እና ደራሲነት የሚታወቁ አንጋፋው የስፖርት ሰው ነበሩ፡፡

ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በተለያዩ ቋንቋዎች የስፖርት ዘገባዎችን በማቅረብ፣ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ በካፍ እና በኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራርነት እንዲሁም በጋዜጠኞች ማኅበር መስራችነት እና አመራርነት ከፍተኛ ግልጋሎት መስጠታቸውን የእግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

“የፒያሳ ልጅ” በተሰኘው መጽሐፋቸው እውቅና ያገኙ ደራሲ ነበሩ።

በኢትዮጵያ ብስክሌት ፌደሬሽን በዋና ጸሀፊነት፣ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ፣ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በዋና ጸሀፊነት፣ በፈረንሳዩ ሌ ኪፕ ጋዜጣ በስፖርት ጋዜጠኝነት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በሚታተመው መጽሄት ዋና አዘጋጅ ሆነው አገልግለዋል።

 

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም የተሰማውን ሀዘን ገልጾ፥ ለቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና አድናቂዎቻቸው መጽናናትን ይመኛል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.