Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስ አስጊ በመሆኑ ማንኛውም ሙስሊም በቤት ውስጥ መስገድ እንደሚችል ምክር ቤቱ ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

ምክር ቤቱ በመግለጫው ማንኛውም ሙስሊም የኮሮና ቫይረስ አስጊ በመሆኑ ከጁምዓ እና ጀመዓ መቅረት በሸርዓ የተፈቀደ መሆኑን አስታውቋል።
በመሆኑንም ህዝበ ሙስሊሙ በየቤቱ መስገድ እደሚችል ነው ምክር ቤት የገለፀው።

በቫይረሱ የተያዘ ወይም የተጠረጠረ ሰው ለጁምዓም ሆነ ለጀመዓ ሶላት እና ለሀይማኖታዊ ትምህርት ወደ መስጊድ እና ህዝብ ወደ ተሰበሰበበት አካባቢ መምጣት እንደተከለከለም ተጠቁሟል።

የጤና ተቋማት እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡትም ምክርና መመሪያ መቀበል እና በስራ ላይ ማዋል ሀይማኖታዊ ግዴታ መሆኑን ምክር ቤቱ በመግለጫው አመልክቷል

የመስጂድ ኢማሞች፣ ኡለሞች እና ዳኢዎች ሙስሊሙን ወደ አላህ እንዲመለስ እና ምህረት እንዲለምን ፣ሰደቃ እንዲሰጥ እና ዱዓ እንዲያደርግ እንዲመልሩ እንጠይቃለንም ብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.