Fana: At a Speed of Life!

በኤርትራ በኮሮናቫይረስ የተያዘ የመጀመሪያው ሰው ተገኝቷል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኤርትራ በኮሮናቫይረስ የተያዘ የመጀመሪያው ሰው ተገኝቷል።

ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ ዛሬ ጠዋት ከኖርዌይ የገባ መሆኑን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የ39 ዓመት እድሜ ያለው ግለሰቡ ኤርትራዊ እንደሆነና በቋሚነት በኖርዌይ እንደሚኖረ የሀገሮቱ የኢንፎረሜሽን ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል ማምሻውን አስታውቀዋል።

ዛሬ በአስመራ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በተደረገ የሙቀት ልኬት ተለይቶ በላብራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ እንደሚገኝበት ከተረጋገጠ በኋላ ግለሰቡ በለይቶ ማቆያ ውስጥ አስፈላጊው የህክምና ክትትል እየተደረገለት ይገኛልም ነው የተባለው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.