Fana: At a Speed of Life!

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት የሞነተሪና ካፒታል ማርኬት ዲፓርትመንት ምክትል ዳይሬክተርና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ።

በውይይቱም በዲፓርትመንቱና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መካከል በውጭ ምንዛሬ፣ በገንዘብ ገበያ፣ በዲጂታል ገንዘብ፣ በውጭ ባንኮች ሬጉሌሽንና ሱፐርቪዥን እንዲሁም በኢንሹራንስ ዘርፍ ሬጉሌሽን ረገድ በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተወያይተዋል።

በተጨማሪም አስፈላጊው የቴክኒክ ድጋፍ ስለሚሰጥበት እና በቀጣይ የሥራ ሂደቶች ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.