Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ለሰራዊቱ ከ214 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመከላከያ ሰራዊት ከ214 ሚሊየን ብር በላይ የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።
 
ድጋፉን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፋይናስ ኃላፊ ወይዘሮ ነጂባ አክመል ለመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሊዊጂ አስረክበዋል።
 
ወይዘሮ ነጂባ አክመል ÷ መከላከያ አሸናፊ የሚሆነው የህዝብ ደጀንነቱ ተጠናክሮ ሲቀጥል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
እስካሁን ሰራዊቱ ከህዝብ ከፍተኛ ድጋፍ አልተለየውም፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ድጋፍም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋለ።
 
ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሊዊጂ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
 
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሠራዊቱን በመደገፍ እያደረገው ያለው ርብርብ በየተሰማራባቸው መስኮች በመድገም ለአገር ሠላም መከበር የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ማለታቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.