Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ሁለት ተጨማሪ  ሰዎች በኮረና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 13፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)በኢትዮጵያ ሁለት ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ እንደተያዙ መረጋገጡን  የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡

በተደረገላቸው የላቦራቶሪ ምርመራ ኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው ሁለት ሰዎች ÷ 28 ዓመት እና የ34 ዓመት ኢትዮጵያውያን  መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የ28 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ በሽታው ሪፖርት ወደ አደረጉ አገሪት ቤልጂየም እና ኔዘርላንድስ ተጉዞ የነበረ እና መጋቢት 5ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ የገባ ነው ተብሏል፡፡

ታማሚው ወደ ሀገር ከገባበት ዕለት ጀምሮ ራሱን በመለየት የጤናውን ሁኔታ ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ÷ የበሽታውን ምልክት በማሳየቱ ባደረገው  ጥቆማ ናሙና ተወስዶ በላብራቶሪ ምርመራ  በኮሮና ቫይረስ  መያዙ መረጋገጡ ተገልጿል፡፡

ሁለተኛው የ34 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ መጋቢት 10 ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሚደረገው የመንገደኞች የሙቀት ልየታ÷ የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች በማሳየቱ በለይቶ ማቆያ እንዲቆይ በማድረግ በላብራቶሪ ምርመራ በኮረና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡

ይህን ተከትሎም በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 11 አድጓል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.