Fana: At a Speed of Life!

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ለመከላከያ ሰራዊት ከ62 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ ለመከላከያ ሰራዊት ከ62 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፉን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ጥሩማር አባተ እና የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ለመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጅ አስረክበዋል።
ከተደረገው ድጋፍ ውስጥ ከ670 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ ምግቦች፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ እና ሌሎች ግብዓቶች መካተታቸው ተመላክቷል፡፡
ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት ውስጥ የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት፣ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አና አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እንደሚገኙበት ተጠቁሟል፡፡
በሳሙኤል ወርቃየሁ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.