Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ የጃክ ማንና አሊባባ ግሩፕ ለሰጠው ድጋፍ አመሰገኑ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  አህመድ የኮቪድ 19ኝ ወረርሽኝን በአፍሪካ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ጃክ ማን እና አሊባባ ግሩፕ ላበረከተው ድጋፍ ምስጋና አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በአፍሪካ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ÷ከጃክ ማን እና አሊባባ ግሩፕ የተላከው  የመጀመሪያውን ዙር የህክምና ግብዓቶች ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ተከትሎ  ነው ምስጋናውን  ያቀረቡት፡፡

ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡት የህክምና ግብዓቶች መካከል የመመርመሪያ፣ የቫይረሱን ሥርጭት የመከላከያና የመቆጣጠሪያ የሕክምና መሣሪያዎች  ይገኙበታል ተብሏል፡፡

መገልገያዎቹ  1 ነጥብ 1 ሚሊየን ቫይረሱን የመመርመሪያ ኪቶች፣ 6 ሚሊዮን የአፍ መሸፈኛ ጭምብሎች እና 60 ሺህ ከቫይረሱ ጋር ንክኪ እንዳይኖር የሚከላከሉ ልብሶች መሆናቸውም ነው የተገለጸው፡፡

እነዚህም መገልገያዎች ኢትዮጵያን ጨምሮ ለመላው አፍሪካ የሚሠራጩ መሆኑንና ለሌሎቹ የአፍሪካ ሀገራት  የማጓጓዝ ሥራው ነገ እንደሚጀምር ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.