Fana: At a Speed of Life!

በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሲንድ ግዛት በጎርፍ ለተጎዱ ፓኪስታናውያን የሰብዓዊ ዕርዳታ አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አምባሳደር ጀማል በከር ከ8 ሺህ ለሚበልጡ የሲንድ ግዛት የጎርፍ ተጎጂዎች ድጋፍ አቅርበዋል፡፡

ድጋፉም ምግብ፣ መድኃኒት፣ መጠለያ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ያካተተ መሆኑን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በጎርፍ አደጋው ከ1 ሺህ 600 በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።

በተጨማሪም 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ቤቶች ሲወድሙ 800 ሺህ የቤት እንስሳት ሞተዋል ነው የተባለው።

ከዚህ ባለፈም የመሠረተ ልማት፣ የትምህርት ቤቶች እና ሌሎች አገልግሎቶች መውደማቸውና መቋረጣቸውንም አምባሳደር ጀማል በከር ጠቁመዋል፡፡

አምባሳደር ጀማል በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.