Fana: At a Speed of Life!

ሲዳማ ቡና እና አርባምንጭ ከተማ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈባቸው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሥነ ምግባር ኮሚቴ በሲዳማ ቡና እና በአርባምንጭ ከተማ የእግር ኳስ ቡድኖች ላይ የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ አሳለፈ፡፡

በሦስተኛ ሣምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ተስተውለዋል ያላቸውን የሥነ ምግባር ግድፈቶች ተከትሎ ነው የሊግ ኩባንያው የዲስፕሊን ኮሚቴ የቅጣት ውሳኔዎችን ያሳለፈው፡፡

በዚህም ሲዳማ ቡና በቅዱስ ጊዮርጊስ በተሸነፈበት ጨዋታላይ የክለቡ ደጋፊዎች የዕለቱን ዳኛ አፀያፊ ስድብ ተሳድበዋል የሚል ሪፖርት በመቅረቡ በክለቡ ላይ የ50 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተላልፏል፡፡

በተጨማሪም አርባምንጭ ከተማ መቻልን በረታበት ጨዋታ የአርባምንጩ ግብ ጠባቂ አቤል ማሞ የተመዘገበ የመለያ ቁጥሩ 1 ሆኖ ሳለ 99 ቁጥር ለብሶ በመግባቱ ክለቡ የ6 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል ተወስኖበታል መባሉን የሊግ ኩባንያው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.