Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሳዳት ነሻ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ ሳዳት ነሻ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ፡፡

አቶ ሳዳት ከዚህ በፊት በፌዴራልና በክልል በተለያየ ኃላፊነት ያገለገሉ ሲሆን÷ ይህ ሹመት እስከተሰጠበት ቀን ድረስ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ።

እንዲሁም ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ተሾመዋል፡፡

 

ዶክተር ቢቂላ ከዚህ በፊት በፌዴራልና በክልል በተለያየ ኃላፊነት ያገለገሉ ሲሆን÷ ይህ ሹመት እስከተሰጠበት ቀን ድረስ በብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው በማገልገል ላይ እንደነበሩ የጽሕፈት ቤቱ መረጃ ያላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.