Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ የሠላም እና የደኅንነት ተግዳሮቶቿን በራሷ መፍታት አለባት – ኃይለማሪያም ደሳለኝ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ ለሠላም እና ደኅንነት ተግዳሮቶች ከውጭ መፍትሄ ከመሻት አስቀድማ በራሷ ለመፍታት መሥራት እንዳለባት የኢፌዴሪ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ገለጹ፡፡

ትናንት የተጠናቀቀው የጣና ፎረም “የአኅጉሪቷ ሠላምና ደኅንነት እንዲረጋገጥ ምላሽ የመስጠት ዐቅም” በሚል ግልጽ የፓናል ውይይት አካሂዷል፡፡

አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ አፍሪካ የመንግስት አስተዳደር ለማስተካከል፣ ብዝሃነትን ለመቀበል እና የራስን ሥልጣን ለማራዘም ቅድሚያ ከመስጠት ይልቅ የዜጎችን ደኅንነት ለማረጋገጥ መሥራት አለባት ብለዋል።

አፍሪካ የምታደርጋቸው የትብብር ሥምምነቶችም አፍሪካውያን ለአፍሪካዊ ችግሮች መፍትሄ እንዳይሆኑ የሚከለክል መሆን የለበትም ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

አፍሪካ ከሌሎች ጋር የሚኖራት አጋርነትም ፍትሃዊ እና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ያማከለ መሆን እንዳለበት አመላክተዋል፡፡

በፓናል ውይይቱ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሀና ቴት፣ በአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ተወካይ ዶክተር አኔት ዌበር እና የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች የሆኑት ባንኮሌ አዴኦዬ ተካፍለዋል፡፡

በጣና ፎረም የመዝጊያ መርሐ-ግብር ላይ በኬኔት ኦሞጄ የተጻፈው “ፊዚቢሊቲ ኦፍ ካፒታሊዝም ኢን አፍሪካ” የተሰኘ የመፅሃፍ ምርቃት እና ሌሎች ሁለት ዝግጅቶች ተካሂደው የ2022 ፎረም ተጠናቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.