Fana: At a Speed of Life!

የክረምት ወራት የወጣቶች በጎፈቃድ አገልግሎት የማጠናቀቂያ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2014 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች በጎፈቃድ አገልግሎት የማጠናቀቂያና የእውቅና መርሐ ግብር በባሕር ዳር ከተማ ተካሄደ።

መርሐ ግብሩ “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ መልዕክት ነው የተካሄደው።

ወጣቶቹ በክረምት የበጎ ፈቃድ ተግባር የአቅመ ደካማ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ቤት ማደስና መሥራት፣ የከተማ ጽዳትና ውበት፣ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ፣ የደም ልገሳ፣ የማጠናከሪያ ትምህርት፣ የትምህርት ቁሳቁሶች የማሰባሰብ ሥራና ሌሎችም የበጎ አድራጎት ሥራዎችን አከናውነዋል።

ከ5 ሚሊየን ወጣቶች በላይ በክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደተሳተፉ የተገለጸ ሲሆን ፥ ከ11 ሚሊየን በላይ የማኅበረሰብ ክፍል የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆኑም ነው የተገለጸው።

በመድረኩም ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ የፌደራልና የክልል የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች መገኘታቸውን የዘገበው አሚኮ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.