Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ህዝቡ ለኮሮናቫይረስ ከሚያጋልጡ ድርጊቶች በመቆጠብ ወረርሽኙን እንዲከላከል የትግራይ ብልፅግና ፓርቱ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  በትግራይ ክልል ህዝቡ ለኮሮናቫይረስ ከሚያጋልጡ ድርጊቶች በመቆጠብ ወረርሽኙን እንዲከላከል የትግራይ ብልፅግና ፓርቱ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ነብዩ ስሁል ሚካኤል ጥሪ አቀረቡ።

ሀላፊው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት ህብረተሰቡ መጨባበጥን በማቆም ፣ እጁን በአግባቡ በመታጠብ እና ጥግግትን በማስወገድ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በመከላከሉ የበኩልን ሚና ሊወጣ ይገበዋል።

ህብረተሰቡ እነዚህን ድርጊቶች በአግባቡ በመፈፀም በራሱ፣ በቤተሰቡ፣ በህብረተሰቡ ብሎም በሀገሩ ላይ ቫይረሱ የደቀነውን ስጋት ለማጥፋት የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ነው ያሳሰቡት።

ሁሉም ሰው በአንድ በኩል በባለሙዎች የሚሰጡ ምክሮችን በአግባቡ በመተግበር  በሌላ በኩል በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለሌሎች ማድረግ የሚጠበቅበትን ድጋፍ በመስጠት የዜግነት ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ነው ያሉት።

በተለይም የቫይረሱን ስርጭት ለማስቆም የሚተላለፉ  ምክረ ሀሳቦችና እና መመሪያዎችን ተቋማት እና ህብርተሰቡ በአግባቡ እንዲተገብሩ አሳስበዋል።

የትግራይ ክልል ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች እና አባላት ከደሞዛቸው በመቀነስም በክልሉ የንፅህና መጠበቂያዎችን መግዛት ለማይችሉ ነዋሪዎች ቁሳቁሶችን እንደሚያበረክቱም ነው አቶ ነብዩ ያስታወቁት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.