Fana: At a Speed of Life!

የእቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ወደ ሙሉ ትግበራ ሊገባ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014 በጀት ዓመት በሙከራ ደረጃ የተጀመረው የእቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ወደ ሙሉ ትግበራ ሊገባ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሙከራ ትግበራውን አፈፃጸም በመገምገም ወደ ሙሉ ትግበራ ለመሸጋገር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ዛሬ ከአጋሮችና ባለድርሻዎች ጋር በአዲስ አበባ ምክክር እየተደረገ ነው፡፡

የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒትር ደኤታ ካሳሁን ጎፌ እንደገለጹት÷ የሙከራ ትግበራው በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በ10 ቦታዎች ላይ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡

በሙከራ ትግበራው አርሶ አደሮች፣ የኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ የግብርና ምርት አቀናባሪዎችና ሌሎችም ምርት አስቀማጮች 60 ሺህ ኩንታል የሚጠጋ የግብርና ምርት ደረጃውን በጠበቀ መጋዘን በማስቀመጥና ደረሰኙን አስይዘው ከባንክ ብድር በመውሰድ ተጠቃሚ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ በሙከራ ትግበራው የተገኙ ስኬቶችና ያጋጠሙ ችግሮች ተገምግመው የመፍትሄ አቅጣጫ ተሰጥቶባቸው ወደ ሙሉ ትግበራ ለመግባት የሚያስችል ስምምነት ላይ ይደረሳል መባሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የእቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ወደ ሙሉ ትግበራ መግባት ያስፈለገው በግብርናው ዘርፍ የሚታየውን የግብይት እና የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.