Fana: At a Speed of Life!

በ100 ሺህ ለሚቆጠሩ ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጥረናል- አቶ ርስቱ ይርዳ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የታሰበውን ያህል ባይሆንም እንደ ክልል በ100 ሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች በማኅበር ተደራጅተው ሥራ እንዲፈጥሩ አድርገናል ሲሉ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ ተናገሩ፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል በደቡብ ክልል ከሚገኙ የካቢኔ አባላት ጋር በአዲሱ የዘርፉ እሳቤ ላይ እየተወያዩ ነው፡፡

አቶ ርስቱ ይርዳ በምክክር መድረኩ ላይ እንደገለጹት÷ ባለፈው ዓመት ባጋጠሙ ችግሮች ሳንንበረከክ ለወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ዐቢይ ጉዳይ ተደርጎ መሠራቱን ነው የተናገሩት፡፡

በአጠቃላይ በክልሉ የታሰበውን ያህል ባይሆንም በገጠር እና በከተማ በ100 ሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች በማኅበር ተደራጅተው ሥራ እንዲፈጥሩ ተደርጓል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸው÷ ሚኒስቴሩ የክህሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳዮችን በአንድ ላይ በማስተሳሰር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ወጣቶችን በአስተሳሰብ እንዲልቁ በማድረግ ያገኙትን ዕድል ሀብት ማፍራት እንዲችሉ መሥራት እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

አዲሱ እሳቤ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ወደ መልካም ዕድል መቀየርን ታሳቢ ያደረገ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በተመሳሳይ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና የክልሉ ካቢኔ አባላት ጋር በዘርፉ አዲስ እሳቤ እና የቀጣይ ሥራዎች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.