Fana: At a Speed of Life!

ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች የ14 ቀናት የለይቶ ማቆያ ግዴታ ተጀምሯል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ኢትዮጵያ በሚመጡ ሁሉም መንገደኞች ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው የ14 ቀናት በልዩ ማቆያ ማዕከል የመቆየት ግዴታ ተጀምሯል።

የጤና ሚኒስቴር ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች በስካይ ላይት እና ጊዮን ሆቴሎች ከዛሬ ጀምሮ ለ14 ቀናት ተለይተው ይቆያሉ ብሏል።

ቆይታቸውም በራሳቸው ወጪ የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል።

ዲፕሎማቶች ደግሞ በኤምባሲዎቻቸው ተለይተው እንደሚቆዩ የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

የትራንዚት ተጓዦችም እስከ ቀጣዩ ጉዟቸው ድረስ በስካይ ላይት ሆቴል ተለይተው ይቆያሉም ነው የተባለው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 30 ሀገራት የሚያደርገውን በረራ በጊዜያዊነት ማቆሙ መግለፁ ይታወሳል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.