Fana: At a Speed of Life!

ኢራን በእንግሊዝ ባለስልጣናት እና ተቋማት ላይ ማዕቀብ ጣለች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን ሽብርተኝነትን ደግፈዋል ባለቻቸው የእንግሊዝ ባለስልጣናት እና ተቋማት ላይ ማዕቀብ ጣለች።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሽብርተኝነትን እና አሸባሪ ቡድኖችን በመደገፍ፣ በማነሳሳት፣ ጥቃትን እና ጥላቻን በመቀስቀስ እና በሰብአዊ መብት ጥሰት በበርካታ የእንግሊዝተቋማት እና ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ ጥሏል።

ሚኒስቴሩ በድረ-ገጹ ባወጣው መግለጫ÷ እርምጃው የተወሰደው ህግና ደንብን መሰረት ባደረገ መልኩ መሆኑን አስታውቋል።

ኢራን እንግሊዝ ውስጥ ሆነው ሁከትና የሽብር ተግባር በመቀስቀስ፣ አሸባሪዎችን በማደራጀት እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመደገፍ ለተፈፀሙ ተግባራት የእንግሊዝን መንግስት ተጠያቂ አድርጋለች፡፡

የብሪታኒያ ብሄራዊ የሳይበር ደህንነት ማዕከል፣ የብሪታኒያ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዋና መስሪያ ቤት፣ ቮላንት ሚዲያ፣ ግሎባል ሚዲያ እና ዲ ኤም ኤ ሚዲያ ማዕቀቡ የተጣለባቸው ተቋማት ናቸው።

በተጨማሪም ፀረ ኢራን አቋም ያራምዳሉ ባለቻቸው እንደ ቢቢሲ ፐርሺያ እና ኢራን ኢንተርናሽናል የቴሌቪዢን ጣቢያዎችም በማዕቀቡ መካተታቸውን መግለጫው ጠቅሷል።

የኢራን ማዕቀብ የብሪታንያ የደህንነት ሚኒስትር ዴኤታ ቶም ቱጌንዳት፣ በባህረ ሰላጤው የእንግሊዝ ወታደራዊ አዛዥ ዶን ማኪኖን ጨምሮ በርካታ ግለሰቦችን ያካተተ መሆኑም ነው የተገለጸው።

ማዕቀቡ የተጣለባቸው ግለሰቦች ቪዛ እንዳያገኙ እና ኢራን እንዳይገቡ የሚከለክል ሲሆን በኢራን ውስጥ ያላቸውን ንብረት እና የባንክ ሂሳብም የሚያግድ መሆኑን የሲ ጂ ቲ ኤን ዘገባ አመላክቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.