Fana: At a Speed of Life!

ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ፑንትላንድ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ የተመራ የፌዴራል እና የሶማሌ ክልል ከፍተኛ ልዑክ ሶማሊያ ፑንትላንድ ገሮዌ ከተማ ገባ።

የኢትዮጵያ ልዑክ ፑንትላንድ ገሮዌ ሲገባ የፑንትላንድ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሰኢድ አብዱላሂ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል፡፡

ልዑኩ በህንድ ውቅያኖስ ላይ የተገነባውና ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥቅምና አገልግሎት የሚሰጠው ዘመናዊው የገራኣድ ወደብ ምርቃት ላይ እንደሚሳተፍ የሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.