Fana: At a Speed of Life!

የብርጋዴር ጀነራል ታደሰ ብሩን ሕይወት የሚዳስስ መጽሐፍ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብርጋዴር ጀነራል ታደሰ ብሩን ሕይወት ታሪክ የሚዳስስ መጽሐፍ ዛሬ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ተመርቋል፡፡

በዙፋን ኡርጋ የተጻፈው “ከደናኔ እስከ ፊንፊኔ” የተሰኘው ይህ መጽሐፍ በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች መዘጋጀቱ ተመላክቷል፡፡

መጽሐፉ ከጀነራል ታደሰ ብሩ 100ኛ ዓመት የልደት በዓል ጋር ተያይዞ የተመረቀ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የባህልና እስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ እንዲሁም የጀነራሉ ቤተሰቦችና የትግል አጋሮቹ ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.