Fana: At a Speed of Life!

በሰው ሃይልም ሆነ በትጥቅ ዘመናዊነት የተላበሰ ሰራዊት እየተገነባ ነው- ዶ/ር አብርሃም በላይ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰው ሃይልም ሆነ በትጥቅ ዘመናዊነት የተላበሰ በአስተሳሰቡም የበቃ ሰራዊት እየተገነባ ነው ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ ገለጹ፡፡

የመከላከያ ሰራዊት ቀንን ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

ሚኒስተሩ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ÷ እየተገነባ ያለው ሰራዊት የኢትዮጵያ ጠላቶች ሰራዊታችን እንዳይዳፈሩት ብቻ ሳይሆን ቀድሞውኑ እንዳያስቡት የሚያደርግና በሰው ሃይልም ሆነ በትጥቅ ዘመናዊነት የተላበሰ እና በአስተሳሰቡም የበቃ ሰራዊት እየተገነባ ነው፡፡

ከጀግናው ህዝብ የወጣው ሠራዊቱ ህዝባዊነቱን ጠብቆ የጀግንነት ታሪክ እየጻፈ መሆኑንም አስረድተዋል።

በፓናል ውይይቱ የኢትዮጵያ ሠራዊት ከየት ወደ የት የሚል አጭር ቅኝት እና የሠራዊት ቀን አከባበር አስፈላጊነት የሚል ጽሁፍ ቀርቧል፡፡

በውይይቱ የቀድሞና የአሁን የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላትና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል፡፡

በሀይለኢየሱስ ስዩም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.