Fana: At a Speed of Life!

ተመድ በዩክሬን የኒውክሌር ፍተሻ ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ በዩክሬን ይፋ ያልሆነ የኒውክሌር ኃይል የማብላላት እንቅስቃሴ መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ የቁጥጥር ቡድኑን ወደ አካባቢው ሊልክ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

እንደ ቢቢሲ ዘገባ የኤጀንሲው የቁጥጥር ቡድን በየትኛው የዩክሬን አካባቢ ፍተሻ እንደሚያደርግ አልተገለጸም፡፡

የተመድ ውስጥ አዋቂን ዋቢ ያደረገው የቢቢሲ ዘገባ ፍተሻ የሚካሄደው ዩክሬን ውስጥ በሚገኙ ሁለት የኒውክሌር ኃይል ማብላያ ጣቢያዎች መሆኑን አመላክቷል።

ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ሃይል ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ራፋዔል ግሮሲ እንደጠቆሙት ፍተሻ ከሚደረግባቸው ጣቢያዎች አንዱ ባለፈው ወርም ተፈትሾ ነበር፡፡

ኤጀንሲው ፍተሻ ለማካሄድ ቀጠሮ የያዘው ዩክሬን “ቆሻሻ ቦምብ” ልትጠቀም ነው የሚለውን የሩሲያን ክስ ተከትሎ ነው ተብሏል።

ይህ ቦምብ ጨረር አመንጪና ቆሻሻ ንጥረ ነገር የያዘ መሆኑ ይነገራል።

ቦምቡ ጥቅም ላይ ከዋለ በፈነዳበት ከ3 አስከ 6 ሜትር ካሬ ክልል ውስጥ በካይ ቆሻሻ የዩራኒየም ንጥረ ነገር በመልቀቅ የሰው ልጆችን ሕይወት አደጋ ውስጥ የመጣል አቅም አለው፡፡

ጨረር አመንጪ ቦምቡ እንደ ኒውክሌር ቦምብ በጥንቃቄ የሚመረት ባለመሆኑና ለመሥራትም ርካሽ ንጥረ ነገር በግብዓትነት የሚጠቀም በመሆኑ “ቆሻሻ ቦምብ” በመባል ይታወቃል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.