Fana: At a Speed of Life!

በመሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 495 ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ በመሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 495 ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው ሀላፊ አቶ ባዩ ከበደ በዞን ደረጃ የዋጋ ጭማሪ ለመቅረፍ የሚያስችል ከንግድና ገበያ ልማት መምሪያና ከዞኑ ፖሊስ መምሪያ የተውጣጣ ዐቢይ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ጤፍ፣ በርበሬ፣ ነጭ ሽንኩርትና ሎሚ የተጋነነ ጭማሪ ታይቶባቸው የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ግብረ ኃይሉ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት የማረጋጋት ሥራ መስራቱን ጠቅሰዋል።

ከነጋዴዎቹ መካከል በ259 ነጋዴዎች ላይ ድርጅታቸውን የማሸግ እንዲሁም 105ቱን ደግሞ ከንግድ ስራ የማገድ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።

በተጨማሪም ለ152 ድርጅቶች የፅሁፍ ማስጠንቀቂያና 6 ድርጅቶች ላይ ክስ ተመስርቶ ጉዳያቸው በህግ እየተጣራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

በተያያዘ ዜና በደብረ ብርሃን ከተማ ከንግድ ፈቃድ ውጭ ከ3 ሺህ ሊትር በላይ የንጽህና መጠበቂያ አልኮል በህገ ወጥ መንገድ ሲሸጥ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማዋ ንግድ ኢንዱስትሪና ገበያ ልማት ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

 

በሰላም አሰፋ

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.