Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ጀርመን ከ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ጀርመን ከ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አድማሱ ነበበ እና በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ብሪታ ዋግነር ተፈራርመውታል።

የድጋፍ ስምምነቱ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ በመደገፍና አዪንቨስትመንት አውዱን በማሻሻል ለሃገር ውስጥ እና ለውጭ የግል ኩባንያዎች የፋይናንስ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም ሃገር በቀሉን የኢኮኖሚ ማሻሻያ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣም ታምኖበታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.