Fana: At a Speed of Life!

በትራፊክ አደጋ የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ ወግዲ ሰቃ-ሽንብራ ‘ውጅቡ’ አካባቢ በተከሰተየትራፊክ አደጋ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በጽህፈት ቤቱ የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ሙሃመድ ኢሣ እንደገለጹት÷ ንብረትነቱ የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የሆነው ተሽከርካሪ ከከላላ ቆርኬ – ወግዲ – መካነ-ሰላም መንገድ የሚሠሩ ባለሙያዎችን ጭኖ ከወግዲ ከተማ ወደ 06 ቀበሌ ሰቃ-ሽንብራ መስሪያ ካምፕ ሲጓዝ አደጋው ደርሷል።
በአደጋው የሦስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በሁለት ሰወች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል ብለዋል፡፡
ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ሕክምና እየተደረገላቸው ነው ማለታቸውን የወረዳው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.