Fana: At a Speed of Life!

የአሸባሪው ህወሓት የሰሞኑ “ከአማራ ህዝብ ጋር ወዳጅ ነን” ፕሮፓጋንዳ አዲሱ የማምታቻ ስልት ነው – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከምስረታው ጀምሮ በአማራ ሕዝብ ላይ የተለያዩ ወንጀሎችን የፈጸመው አሸባሪው የህወሓት ቡድን አዲስ የማምታቻ ስልት ለመከተል እየሞከረ መሆኑን ምሁራን ገለጹ፡፡

ምሁራኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ የአማራ ሕዝብን በጠላትነት ፈርጆ ጥፋቶች መፈፀሙ ሳይረሳ ወዳጅ በማለት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እያሰራጨ ነው፡፡

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ጥናት ተመራማሪው ንጋቱ አበበ እንደገለጹት÷ የሽብር ቡድኑ ከፖለቲካ ፕሮግራሙ ጀምሮ ሕዝብን በጠላትነት ፈርጆ ሲንቀሳቀስ ነበር፡፡

ለዚህም ለፕሮፖጋንዳነት በሚጠቀምባቸው የኪነጥበብ ሥራዎቹ እንዲሁም በድርጊቱ ጥላቻው መንፀባረቁ ማሳያ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስ መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ዳምጠው ተሰማ በበኩላቸው÷ የአሸባሪው ህወሓት አባላት በአማራ ሕዝብ ላይ የሐሰት ትርክት በመፈብረክ ዒላማ እንዲሆን አድርገውታል ብለዋል፡፡

በአማራ ክልል ወረራ በፈፀመበት ወቅት በግድያ፣ ሕዝብን በማዋረድና የክፋት ተግባር በመፈጸም ጠላትነቱን በግልጽ አሳይቷል ነው ያሉት፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቅርቡ የሽብር ቡድኑ ሕዝብን ለማታለል የዐይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ መንገድን እየተከተለ መሆኑን ነው ምሁራኑ የተናገሩት፡፡

ተግባሩ ከሕዝቡ የተደበቀ አይደለም ያሉት ምሁራኑ÷ ህብረተሰቡ አንድነቱን በማጠናከር ሀገሩን ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል፡፡

በአፈወርቅ እያዩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.